በአማርኛ ቋንቋ ኢ-አፍፈት የሆኑ ተማሪዎች ድርሰት ሲፅፉ የሚፈፅሟቸው ስነልሳናዊ ስህተቶች ፍተሻ (በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የ9ኛና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

Authors

Abstract

አጠቃሎ 
ይህ ጥናት ያተኮረው በአማርኛ ቋንቋ ኢ-አፍፈት የሆኑ ተማሪዎች ድርሰት ሲፅፉ የሚፈፅሟቸው ስነልሳናዊ 
ስህተቶች ፍተሻ (ኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የ9ኛና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት) በሚል ርእስ 
በሚሰራው ጥናት ላይ ነው፡፡ በዞኑ ውስጥ  በአራት ወረዳዎች የሚማሩ በአማርኛ ኢአፍ ፈት የሆኑ ሁልት መቶ 
ኣርባ (240)ተማሪዎች እና በየትምህርት ቤቱ ኣማርኛን የሚያስተምሩ ስምንት(8) መምህራን እንዲሳተፉ 
ተደርጓል፡፡ የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ባሁኑ ወቅት በአማርኛ ቋንቋ አፋቸውን ያልፈቱ የአማርኛ ቋንቋን የሚማሩ 
ተማሪዎች የሚፈፅሙት ከጽኅፈት ጋር የተያያዙ ስህተቶችን ነቅሶ በማውጣት ላይ ያትኮረ ነው፡፡  ጥናቱ 
መጠናዊ እና ኣይነታዊ የኣጠናን ዘዴዎች በመቀየጥ የተጠቀመ ሲሆን የኣጠናን ስልቱም ቅኝታዊ ገላጭ ነው፡፡ 
መረጃዎች የተሰበሰቡት፤ ተጠኚ ተማሪዎችን አንቀጽ በማጻፍ ስህተቶችን ነቅሶ በማውጣት፣ የጽሁፍ 
መጠይቆችን በማስሞላት፣ ተማሪዎችን እና መምህራንን ቃለ መጠይቅ በመጠየቅ እና የቡድን ወይይት 
በማከናወን ነው፡፡ በሁሉም መረጃ መሰብሰቢያዎች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ተጠኚ ተማሪዎች 
ከፍተኛ የሆነ የጽህፈት ችግር ኣለባቸው፡፡ የኣናባቢ እና የተነባቢን ጥምረት በተገቢው መንገድ ኣይጠቀሙም፣ 
ቃላትን በኣውዳቸው ያለመጠቀም፣ ሰዋስዋዊ ስህተቶች እና በርካታ ተማሪዎች ምንም መጻፍ ኣለመቻል 
ታይቶባቸዋል፡፡ በጽህፈት ወቅት የሚፈጸሙ ስህተቶች ተግባቦት ከማወክም አልፈው ምን ለማለት እንደተፈለገ 
ፍቺውን መረዳት የሚያዳግቱ ወይም ወዳልተፈለገ ተግባቦት የሚያደርሱ ናቸው፡፡ ስለዚህ የአማርኛው ቋንቋ 
ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ትኩረት ተሰጥቶት በጥሩ ሁኔታ የሚሰጥበትን በማመቻቸት፤ በቋንቋው 
የሚማሩ ተማሪዎችም የስነልሳን እና የክሂል ትምህርቶችን በተለየ ሁኔታ በጥልቀት እና በዝርዝር እንዲማሩ 
ቢደረግ ችግሩ በከፍተኛ መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ በቋንቋውም በተገቢው ሁኔታ ሊገለገሉበት ይችላሉ፡፡ 
ቁልፍ ቃላት፣ ኢ-አፍፈት፣ ስነልሳናዊ ስህተቶች፣ የጽህፈት ችግር ፣ተግባቦት ማወክ

Downloads

Published

2026-11-18