ፍካሬ ፍቅር ወአንድነት/ዘፖለቲካ/ በአደፍርስ
Abstract
አኅጽሮተ ጥናት
“አደፍርስ” ከቅድመ አብዮቱ መባቻ ልብ ወለድ መኻል አንዱ ነው፡፡ይህ ልብ ወለድ ዐያሌ የነገረ
ሰብእ ጉዳዮችን በውስጡ አምቆ የያዘ “ዘመን ተሻጋሪ” ልብ ወለድ ነው፡፡ይህ ጥናት ከዚህ ልብ ወለድ
የንባብ አሐዶችን መርጦ በመውሰድ ማኅበረ ለፖቲካ ሒሳዊ ንባብ ማቅረብን ዐቢይ ዐላማው
አደርጓል፡፡ምርምሩ በቴክስታዊ የንባብ ሐዶችን እየታገዘ ከማኀበረ— ፖለቲካዊ እስቦች አንጻር
አሐዶችን ፈክሯል፡፡ በጥናቱ ሄደት ውስጥም ቴክስታዊ አሐዶችን የመለየት፣ የማጣመር፣ የማዋቀር
እና የመለወጥ ሒሳዊ የንባብ ደረጃዎች ተከናውነዋል፡፡ዋና ሥልቱ ግን ፖለቲካዊ አንድምታና ፍካሬን
ማቅረብ ነው፡፡ ዐዲሱየታሪክ ሥነ-ጽሑፋዊ ሂስ ንድፈ ሐሳብን በመከተል በመቼቱ ኹነት፣ በገጸ
ባሕርያቱ ተዋሥዖ እና በኪነታዊ ሥነ-ጽሑፍ ሥልቱ ውስጥ ኹለንተናዊ ፍካሬን ለማቅረብ
ሞክሯል፡፡ምርምሩ ዐይነታዊ አንጻር ተከትሎ በጥብቅ ሒሳዊ ንባብ ተካኺዷል፡፡ ርእዮተ ዓለማዊ
መሻቶችና ቅራኔዎች ከተውኔታዊ ድርጊቶች ተጣጥመው በልብወለዱ ትልማዊ ጉዞ እስከ መጨረሻ
የማይፋቱ ጉዳዮች ናቸው:ስለዚህም በድርሰቱ ውስጥ ፍቅርና አንድነት፣ የለውጥ ፍላጎት ማኅበራዊ
ተሐድሶና ግለሰባዊ እሳቤ እርስበርስ ተጋምደው የቀረቡ ጭብጦች ናቸው:: በዚህም ውስጥ የብሔረ
መንግሥት ግንባታው እውን የሚኾንባቸው ፍቅርና አንድነት ሠምረውና አብረው ዐቢይ ጭብጥነት
ግዘፍ ነሥተው ቀርበዋል::
ቁልፍ ቃላት፡
አደፍርስ፣ “ዘመን ተሻጋሪ”፣ በቴክስታዊ የንባብ ሐዶች፣ ሥነ-ጽሑፋዊ ሂስ ፣ተውኔታዊ
ድርጊቶች