6. የሀገረሰባዊ ህክምና ምላሽ ለኮቪድ 19 (በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ተተኳሪነት)

Authors

  • sjsisadmin sjsisadmin

Abstract

ይህ ጥናት በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘውን የማኅበረሰብ ክፍል ማዕከል ያደረገ ሲሆን ከፎክሎር
ዘውጎች ውስጥ በሀገረሰባዊ ልማድ (Folk-custom) ስር የሚጠናውን ሀገረሰባዊ ሕክምና (Folk
medicine) የሚመለከት ነው። ጥናቱ ይዞት የተነሳው ዋና ዓለማም የማኅበረሰቡን የወረርሽኝ
መከላከያ ዘዴዎችን፣ ስልቶችና የመግቻ መንገዶችን በመቀመር ለኮቪድ-19 በሽታ ሀገረሰባዊ
መከላከያ ስልቶችን መጠቆም እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማመላከት ነው፡፡ የጥናቱ ዓላማ ግብ
እንዲመታና የምርምር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ከባህል መድኃኒት አዋቂዎች፣ ከባህሉ
ባለቤቶች፣ ከሃይማኖት አባቶች እና ከጥንታዊ መጽሐፍት በመዛግብት ዳሰሳ፣ በቃለ መጠይቅ እና
በውይይት አማካይነት መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች በይዘታቸው ወይም በርዕስ
ጉዳያቸው ተደራጅተው ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ ትንተናው የተደራጀበት መንገድም ማኅበረሰቡ
ስለጤና፣ ህመም እና ኮቪድ 19 ያለውን ግንዛቤ፣ በቀደሙት ዘመናት የተከሰቱ ወረርሽኞች
የፈውስና የመከላከያ መንገዶች፤ ኮቪድ 19ን ለመከላከል እየተተገበሩ ያሉ ስልቶች ከማኅበረ ባህላዊ
ዳራ ጋር ያላቸው ስምረት እና ሀገረሰባዊ የህክምና ዘርፉ ኮቪድ 19ን ለመከላከል የሚያበረክተው
አስተዋጽኦ በሚል ነው፡፡ በጥናቱ ግኝትም የማኅበረሰቡ ቀደምት የወረርሽኝ መከላከያ መንገዶች
ናቸው ተበለው የተቀመጡት አካባቢን ለቆ ለጊዜው መሄድ፣ ባህላዊ ክትባት፣ ውሸባ/ቀሳ፣
ኃይማኖታዊ ክዋኔዎች፣ ጭሳጭሶች እና መልእክት የመለዋወጥ ስርዓቱ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በዚህ መነሻነትም ለኮቪድ 19 መከላከያነት የቀረቡት ስልቶች ለሰሜን ሸዋ ማኅበረሰብ አዲስ
ያልሆኑና ከአሁን በፊትም ሲተገበሩ የነበሩ ናቸው።

Downloads

Published

2024-10-28