5. የምዕተ ዓመታት የኣማርኛ ኣናባቢዎች ገለጻ ዳሰሳ

Authors

  • sjsisadmin sjsisadmin

Abstract

ይህ ጥናት በአማርኛ ቋንቋ ኣናባቢ አይነቶችና ባህሪያት ገለጻ ላይ ትኩረት በማድረግ የተሰሩ
ጥናቶችን በመቃኘት የተከናወነ ነው፡፡ ጥናቱ ቅኝታዊና ገላጭ የሆነ ስነልሳናዊ ጥናቶች
ትንተና ነው፡፡ የጥናቱ ትኩረት በኣማርኛ ኣናባቢ አይነትና ባህሪ ላይ የተለያዩ የስነልሳን
ባለሙያዎች የሰሯቸውን የተለያዩ ስራዎች ቃኝቶ በገለፃዎች ላይ ስላለው ልዩነት ማብራሪያ
ከመስጠቱም ባሻገር ፣ የኣማርኛን ኣናባቢ አይነትና ባህሪያት በተመለከተ ወቅታዊ ሁኔታን
ያገናዘበ ሙያዊ አስተያየት መስጠት ነው፡፡ መረጃዎች የተሰበሰቡት በአማርኛ አናባቢዎች
ላይ ከመቶ ዓመታት በላይ የተደረጉ ጥናቶችን በመፈተሸ ነው፡፡ ከ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን
መግቢያ ጀምሮ እንደ ኣውሮጳዊያን ዘመን አቆጣጠር ከአምበስትር 1908 እስከ ሚካኤል እና
ሌሎቹ (2016) በተለያዩ ጊዚያት በተለያዩ የስነልሳን ተመራማሪዎች የተሰሩ የኣማርኛን
ኣናባቢ የተመለከቱ ስራዎች ኣበይቱ ሃያ ኣራት ያህሉ ተዳሰው ቀርበዋል፡፡ በኣጥኝዎች
መካከል የኣማርኛ አናባቢ ገለጻን በተመለከተ ልዩነቶች መኖራቸው ተስተውሏል፡፡ በብዙዎቹ
ጥናቶች የአማርኛ አናባቢ አይነትና ባህርያት እንዲሁም ስርጭትና ቅንጂት ስነልሳናዊ
የሙያ ገለጻ ተደርጎባቸዋል፡፡ ከአማርኛ አናባቢዎች ውስጥ ብዙዎቹ ማለትም ኣራቱ (ኡ፣
ኦ፣ ኢ ና ኤ) ከቃል መጀመሪያ በአብዛኛው ባይከሰቱም፣ በየትኛውም የአማርኛ ቃል ስደራ
ወቅት በሁሉም ቦታ (ከቃል መጀመሪያ፣ መካከልና መጨረሻ) ሊገኙ የሚችሉ ሶስት
አናባቢዎችን (እ፣ኧ እና ኣ) የተባሉትን ጨምሮ፤ ሰባት ኣናባቢ ድምጸ ልሳናት አሉት፡፡
ይሁን እንጂ በተለያዩ የአማርኛ ዘዬ ተናጋሪዎችም ይሁን ኣማርኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ
በሚናገሩ ሰዎች መካከል ያለው የንበት ልዩነት በጠራ ሁኔታ ሊገለጽ አልቻለም፡፡ በዚህ
ጥናት የተዳሰሱት፣ በተለያየ ወቅት፣ በአማርኛ አናባቢ ላይ የተደረጉ ስነልሳናዊ ገለፃዎችም
ልዩነት እና አሻሚነት ተስተውሎባቸዋል፡፡ የኣማርኛ ኣናባቢዎች ሁለት ብቻ ናቸው ከሚሉት
ጀምሮ ሃያ የሚያደርሱትም ኣልታጡም፡፡ ልዩነቱ እና አሻሚነቱ በስፋት ጎልቶ የሚታየዉ
በተለይ በሁለቱ (/ኧ/ እና /እ/ ኣናባቢዎች ላይ ነው፡፡ ስለዚህ የስነልሳን ትምህርት፣
በተለይም ሙከራዊ ስነ ድምጽ(experimental phonetics) በከፍተኛ እምርታ ላይ ያለበት
ወቅት በመሆኑ፤ መረጃዎችን በዘመናዊ የስነልሣን ጥናት መሠረት፣ በመሳሪያዎች
በመታገዝ፣ ከተለያዩ የቋንቋው ዘዬዎች አፈ ፈት የሆኑ ተናጋሪዎች ሠፊ መረጃ
በመሰብሰብ፣ ወቅቱ በሚፈቅደው ቃለነቢብ በመታገዝ ጥልቅ ሳይንሳዊ ጥናት በማድረግ
ለቋንቋው አናባቢዎች ግልጽና የማያሻማ መግለጫ መስጠት ይገባል፡፡ ይህም በቋንቋና
ስነልሳን ተማሪዎች እንዲሁም በተናጋሪዎች ላይ የሚከሰተውን ብዥታ ሊያስወግድ
ከመቻሉም በላይ የኣማርኛ ቋንቋን አናባቢዎች ገለጻ በኣግባቡ ለማስተማር ያስችላል፡፡

Downloads

Published

2024-10-28